News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Nov 30, 2022 3.8K views

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን በሚገባ በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ብቃት ያላቸውን ዜጎች ማፍራት እንድችሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት መስጠት እየደገፋቸው መሆኑ ተገለጸ፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ ዶ/ር እዮብ አየነው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን በሚገባ በማስጠበቅ ሁለንተናዊ ብቃት ያላቸውን ዜጎች ማፍራት እንድችሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት በመስጠት እየደገፋቸው መሆኑን ጠቅሰው ድጋፎቹም
ድጋፎቹም የረጅም ጊዜ የትምህርት እድል፣አጫጭር ሥልጠናዎችንና ሌሎችንም የሥራ ላይ ድጋፎችን የሚያካትት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር እዮብ አክለውም ተቋማቱ የሚመለከታቸውን ደንብና መመሪያ አክብረው እንዲሠሩ እና ተገልጋይ ህብረተሰቡም ከመገልገላቸው በፊት ስለተቋማቱ ህጋዊነትና ውስጣዊ ብቃት በበቂ መረጃና ማስረጃ ላይ ተሞርክዘው በመለየት መገልገል ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰው በተጨማሪም ህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት የሚሰጡትን ተቋማት በማበረታታት እና ህገ-ወጥ ሥራ የሚሰሩትን በመገሰጽና በማጋለጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ሥልጠና በጥናት በተለዩና ፍላጎትን መሠረት ባደረጉ አራት ርሶች ላይ ሲሆን እነሱም በመሪነትና አመራር፡በስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት በሀብት አጠቃቀምና በሌሎችም ርዕሶች ላይ መሆንና በቀጣይ በጉድኝት በተከፋፈለ መልኩ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች ለሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች የሚሰጥ መሆኑን ተመላክቷል፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ስርጸት ዴስክ ሀላፊ ዶ/ር ሰራዊት ሀንድሶ በሥልጠናው መድረክ ላይ ተገኝተው ስለስትራቲጂክ እቅድ አዘገጃጀት ባሰለጠኑበት ወቅት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመማር ማስተማር ለሀገሪቱ የሰው ኃይል ልማት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ በቴክኖሎጂ ሽግግር፡በምርምርና በሀገር በቀል ዕውቀት መደገፍ እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል።
በቢሾፍቱ ከተማ በተሰጠው ሥልጠና ላይ በአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
Recent News
Follow Us