News Detail
Nov 30, 2022
3.6K views
የስራ ሀላፊዎች እምነት፣ቁርጠኝነትና ድርጊት ህግን መሰረት ያደረገ የመንግስት አስተዳደር ከማሳደግ አንጻር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ
ህዳር 14/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እስከ ቡድን መሪዎች ላሉ ሀላፊዎች በአስተዳደራዊ ውሳኔ አሰጣጥና መመሪያ አወጣጥ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ይበልጣል ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ሃላፊዎች በተዘጋጀ ስልጠና ላይ እንደተናገሩት የአሰራር ህጎችንና መመሪያዎችን አውቆና ተረድቶ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ስራን በጥራት በመስራት ለላቀ ተግባር መነሳሳት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ስራ አስፈፃሚው አያይዘውም በየጊዜው የሚወጡና የሚሻሻሉ መመሪያዎችንና ደንቦችን መረዳት ከስራችን ስኬት በተጨማሪ መብትና ጥቅሞቻችንን በማስጠበቅ በግል ህይወታችን ስኬት የላቀ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
በፍትህ ሚኒስቴር የፌደራል ህጎች ተፈጻሚነት መከታተያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትብለጥ ቡሽራ በስልጠናዉ ወቅት እንደገለጹት የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እምነት፣ቁርጠኝነትና ድርጊት ህግን መሰረት ያደረገ የመንግስት አስተዳደር ከማሳደግ አንጻር ትልቅ ፋይዳ እንዳለዉ አበክርው ተናግረዋል።
በስልጠናዉ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ ስራ አስፈጻሚዎች፣ዴስክ ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡