News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 13, 2022 2.6K views

በህዳሴ ግድብ፣ አረንጓዴ አሻራ እና የስንዴ ምርት ያየነውን ውጤት በትምህርት ጥራት እንደግመዋለን - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመላው አገሪቱ የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ፈታኝ መምህራንን በበየነ መረብ አግኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፈተና ስርዓቱ በባለፋት አመታት ባልተገባ ሁኔታ የተለያዬ ፍላጎት ባላቸው አካላት ለችግር የተጋለጠ እንደነበር ጠቅሰው ዘንድሮ ከዚህ ችግር ለመላቀቅ በተደረገው ጥረት የመምህራን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሃላፊነታቸውን በታማኝነት እንዲወጡ አደራ ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው እስካሁን በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የነበረው ዝግጅት የተሳካ እንደሆነ ገልጸው በተጀመረው መንገድ በስኬት እንዲጠናቀቅ ፈታኝ መምህራንን ጨምሮ በሂደቱ ድርሻ ያላቸው አካላት በመተባበርና በፍጹም የሃላፊነት ስሜት እንዲሰሩ አሳስበዋል ።
አሁን በሁሉም 12ኛ ክፍል ፈታኝ ዩኒቨርስቲዎች ለፈታኞች ገለጻ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ የተፈታኞች ገለጻ የሚደረግ ይሆናል።
Recent News
Follow Us