News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 13, 2022 2.5K views

ከ900ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይፈተናሉ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከመስከረም 30 ጀምሮ በሁለት ዙር በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና 976ሺህ 18 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

 

ይህንንም ተከትሎ በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚፈተኑ ተፈታኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት በ300 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተነግሯል።
በጸጥታና በሌሎችም ምክንያቶች ፈተናውን መውሰድ የማይችሉ ተማሪዎች ደግሞ በአንድ ወር ጊዜው ውስጥ በሁለተኛ ዙር በተመሳሳይ ፈተናውን እንደሚወስዱ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ህብረተሰቡም መንግስት የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ የወሰደውን እርምጃ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልጆቻቸውን ወደፈተና ጣቢያዎች ከመላክ ጀምሮ በፈተናው የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይመጡ በመከልከል ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፋንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) በበኩላቸው ፈተናው በዩኒቨርስቲ መሰጠቱ የፈተና ስርቆትን እንደሚያስቀር ገልፀዋል።
ለሂደቱ ስኬታማነትም ተማሪዎች ፣ ወላጆች፣ የደህንነትና ጸጥታ አካላት፣ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤትና ትምህርት ቤት አመራሮች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ተቋማት፣ የሚዲያ አካላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጉዳዩ የተሻለች አገርን የመገንባት በመሆኑ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሁለት ዙር በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
Recent News
Follow Us