News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Sep 29, 2022 2.4K views

ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች የትምህርት ሁኔታ ለማሻሻል ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ተጠቆመ

(መስከረም 13/2015 ዓም ) 3ኛው አገር አቀፍ የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ  ፋንታ ማንደፍሮ ( ዶ/ር ) ጉባኤውን ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልእክት የልዩ ፍላጎት  ያላቸው ተማሪዎችን የትምህርት ሁኔታ ማሻሻል የሁሉንም ባለድርሻዎች ርብርብ ይሻል::

በመሆኑም ሁሉም ባለድርሻዎች ለልዩ ፍላጎትና ለአካቶ ትምህርት መሻሻል  ቀጣይነት ያለው ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ደኤታው  አስገንዝበዋል፡፡

በ6ኛው የትምህርት ልማት  ዘርፍ መርሃ-ግብር ለልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት  በመስጠት ከባለዘረፈ ብዙ ጉዳቶች አንዱ ሆኖ እንዲካተት  መደረጉንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ትምህርት ትኩረት የሚሰጠውና ተግባራዊ የሚያደርገው ዓለም አቀፍ ስምምምነቶችን ስለተቀበለ ብቻ ሳይሆን    ያላቸውን  እምቅ ክህሎትና ችሎታ ተጠቅመው የሀገር ልማትና እድገት ላይ  የራሳቸውን አሻራ እንዲያስቀምጡት ጭምር ነው ብለዋል፡፡

በፊላንድ መንግስትና  በዓለም ባንክ ትብብር በዘርፉ በተሰራው ስራም በአንደኛ ደረጃ የልዩ  ፍላጎት ተማሪዎች ተሳትፎ  በ2006 ዓ.ም. ከነበረበት ሰባ ሺ አራት መቶ ሰባ ሰባት በሰባት ዓመታት ውስጥ  በ3 እጥፍ በማደግ በ2013 ዓም. ወደ 233ሺ 310 ማሳደግ መቻሉንም አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ   የፊንላንድ  አሜባሲ  የትምህርት አማካሪ  ፒኣ ኮርፒነን  በበኩላቸው በኢትዮጵያና በፊንላንድ መንግስታት ትብብር  በአካቶ ትምህርት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም በአሁኑ ጊዜ ከ90 ሺህ በላይ አካል ጉዳተኛ ህጻናት የትምህርት እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተቁመው ይህም በእቅድ ከተያዘው 24 ሺ አካል ጉዳተኛ ህጻናት በ3 እጥፍ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በልዩ ፍላጎት/ በአካቶ ትምህርት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ ቢሆንም አሁንም ገና ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅ ሚስ ፒኣ ጨምረው አስገንዝበዋል፡፡

ጉባኤው በሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በልዩ ፍላጎትና /አካቶ ትምህርት አተገባበር ዙሪያ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

በጉባኤው ላይ ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች፣ ከአካል ጉዳተኛ ማህበራት እና ሌሎችም ጉዳይ የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Recent News
Follow Us