News Detail
Mar 04, 2021
254 views
ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ወደ ትግበራ ገባ።
የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ያግዛል የተባለ እና ትምህርት ቤቶች ደረጃውን የጠበቀ የመጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት እንዲኖራቸው የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል።
መመሪያውን የትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒሴፍና ፒ ኤስ አይ በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ውስጥም እየተተገበረ መሆኑ ተገልጿል።
ሰነዱን ለማዘጋጀት ዩኒሴፍ በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን መመሪያው የጥገና ፣ የዲዛይንና የግንባታን መመሪያንም የያዘ ነው።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዬን ማቲዮስ መመሪያው የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እንደሚያግዝ ገልፀው መመሪያው እንዲዘጋጅ ላደርጉት አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር፣ የዩኒሴፍ እና የፒ ኤስ አይ ሃላፊዎች በተገኙበት የተዘጋጀውን መመሪያ ርክክብ ተደርጓል።