News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Dec 23, 2020 943 views

ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራው ቢጀመርም በርካታ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት አልቻሉም ተብሏል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በበይነ መረብ መክረዋል።

ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ስራ ድጋሚ የተጀመረ ሲሆን አሁንም ወደ ትምህርት ገበታቸው ያልተመለሱ ተማሪዎች እንዳሉ ተነስቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አሳስበዋል።

ትምህርት ላይ የሚሰሩ አጋር አካላትና ከትምህርት ዘርፍ ውጭ ያሉ ተቋማትም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

"ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ" በሚል ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው የመመለስ ዘመቻም ይጀመራል።

Recent News
Follow Us