እንኳን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ድረ ገጽ በደህና መጡ!

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ ተቋም ነው።

የቅርብ ጊዜ ዜናችን

የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን እና ክስተቶችን ያንብቡ

የሀገር ውስጥ ዜና

በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ የልዑካን ቡድን በፊንላንድ ጥናታዊ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

ከፊላንድ መንግስት በተላከላቸው ግብዣ መሠረት በክቡር ሚኒስትሩ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በፊንላንድ ጥናታዊ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።
በዚህ ጉብኝትም የትምህርት ሚኒስትሩን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወትና የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እኩኝ ኡኬሎ እየተሳተፉ ይገኛል።
የልዑካን ቡድኑ በቆይታው ከፊንላንድ የትምህርትና ባህል ሚኒስትር፣ ከፊላንድ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ የትምህርት ማዕከል፣ እንዲሁም ከሂልሲንኪ ዩኒቨርሲቲና ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችን ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል።
በዚህ ጥናታዊና የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ወቅትም በኢትዮጵያና በፊላንድ የትምህርት ተቋማት ሊኖር ስለሚገባው ትብብር እና የፋይናንስ ድጋፍ ተጠናክሮ በሚቀጥልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Nov 07, 2025 38
የሀገር ውስጥ ዜና

በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራ ልዑካን ቡድን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፏል።

በትምህርት ሚኒስትሩ የተመራ የልዑካን ቡድን አባላት በሳማርካንድ፣ ኡዝቤኪስታን ሪፐብሊክ በተካሄደው 43ኛው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፎ አድርጓል።
በዚህ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) 43ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ክቡር ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በዩኔስኮ ዘርፎች ያከናወነችውን ተግባራት አብራርተዋል።
በዚህም ከትምህርት፣ ከባሕል፣ ከአየር ንብረት ለውጥ እና ከብዝሃ-ሕይወት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው ያሉ ሥራዎችን ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡
አያይዘውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የተነደፉ ስትራቴጂዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው ይህ የዩኔስኮ ጠቅላላ ጉባኤ በትምህርት፣ በሣይንስ፣ በባህል፣ ተግባቦትና መረጃ ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ፤ አባል ሀገራትን ለመደገፍ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መድረክ እንደሆነም ተጠቁሟል።
ክቡር ሚኒስትሩ ከጉባኤው ጎን ለጎንም ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር የሚያስችሉ ውይይቶችን አድርገዋል።

Nov 07, 2025 30
የሀገር ውስጥ ዜና

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሥርዓተ ትምህርት ውጤት ተኮር እንዲሆን ክለሳ እየተደረገበት መሆኑ ተገለጸ፤ ‌‎የሚከለሰው ስርዓተ ትምህርትም በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተልዕኮ መሰረት ባደረገ መልኩ ስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የዩኒቨርስቲዎቹን ስርዓተ ትምህርት ውጤት ተኮር አድርጎ መከለስ ያስፈለገው የቀድሞዎቹ ስርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ያልዋጁና ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር በአግባቡ ያልተቃኙ በመሆናቸው ነው።
‎አዲሱ የውጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት ተመራቂዎች በትምህርት ፕሮግራሞቹ መጨረሻ ሊኖራቸው የሚገባውን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት በአግባቡ የፈተሸ መሆኑን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡
‌‎የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ነገዎ በበኩላቸው ውጤት ተኮር የሆነው ስርዓተ ትምህርት ሙያና ተግባር ተኮር መሆኑን ጠቅሰው ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ምሩቃንን ማፍራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።‎
በሁለት ዙሮች እስካሁን 55 የትምህርት ፕሮግራሞች መከለሳቸውን አንስተው እስከ ዓመቱ መጨረሻም ከ80 የሚበልጡ ፕሮግራሞች እንደሚከለሱ አብራርተዋል፡፡
አዲስ የተከለሱት የትምህርት ፕሮግራሞች በ2018 የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲ የገቡ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ እንደሚደረጉም ተጠቅሷል።
‎የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ በሱፈቃድ ሃይለማርያም ለስርዓተ ትምህርት ክለሳው ለቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች መሰረታዊ የሆኑ የተማሪዎች ብቃት መለኪያ (competency) ዝግጅት መከናወኑን ጠቁመዋል።

Nov 05, 2025 99
የሀገር ውስጥ ዜና

በመምህራን የትምህርት ዝግጅትና ልማት ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

“Educators shaping futures" በሚል መሪ ቃል በመምህራን የትምህርት ዝግጅትና ልማት ላይ ያተኮረ አለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
ትምህርት ሚኒስቴር ከአለም ባንክና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ ባዘጋጀው በዚህ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ የበርካታ ሀገራት የትምህርት ባለሙያዎችና ስራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ ለትምህርት ጥራት መሳካት መምህራን ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ መምህራንን ማብቃትና መደገፍ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና መሆኑን አመላክተው በዚህም የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
መንግስት ለትምህርቱ ዘርፍ በሰጠው ትኩረት በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንና ከነዚህም አንዱ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮችን አቅም መገንባት መሆኑን አንስተው መምህራኑ እውቀትን ከማስተላለፍ ባለፈ ትውልዱ የጽናትና ተስፋ ተምሳሌት ሆኖ እንዲቀረጽ የሚረዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመከናወን ላይ ያሉት የሪፎርም ስራዎችም የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ከሀገራዊ የልማት ፕሮግራሞች ጋር በማዋደድ እውቀት መር ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረጉ ጥረቶችን የሚደግፍ መሆናቸውን ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል።
መሠል አለም አቀፍ ምክክሮች ልምድና አሠራሮችን ለማወቅና ለመለዋወጥ በር የሚከፍቱ በመሆኑ ለዝግጅቱ መሳካት ጥረት ያደረጉ ወገኖችንም አመስግነዋል።
የአለም ባንክ ዲቪዥን ዳይሬክተር ሜሪያም ሳሊም በበኩላቸው "Universal Education" ን በ2030 ለማሳካት ዓለማችን ተጨማሪ 44 ሚሊየን መምህራን የሚያስፈልጋት መሆኑን የገለጹ ሲሆን ለዚህም አዳዲስ መምህራን ወደ ዘርፉ የሚቀላቀሉበትን አማራጮች ማብዛት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የወደፊቱ ትውልድ የሚወሠነው አሁን ላይ ባለን የመምህራን ዝግጅት፣ ብቃትና ልማት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ መምህራንን ማብቃትና መደገፍ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በጉባኤው 271 ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡእና ከ150 በላይ የሚሆኑ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የዘርፉ ተዋንያኖች የተሳተፉበት መሆኑም ተመላክቷል።

Nov 04, 2025 89
የሀገር ውስጥ ዜና

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት እንዲሰጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፤ የ2016 ምሩቃን የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ከተያዘው ጥቅምት እስከ መጪው ሚያዚያ ወር እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
በመደረኩ የተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ የከፍተኛ ትምህርት ተማራቂዎች የመዳረሻ ጥናት የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ፕሮግራሞቻቸውን የመዳረሻ ጥናት ካላካሄዱ ምን እየሰሩ እንደሆነ ለማወቅ እንደሚቸገሩና በገበያው የማይፈለግ የሰው ሀብት ሊያሰለጥኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ትኩረት በመስጠት በትምህርት ፕሮግራም ደረጃ ወጥ በሆነ መንገድ ሊሰሩ እንደሚገባ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ ህይወት በበኩላቸው የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) ለፖሊሲ ውሳኔ ፣ ለስርዓተ ትምህርት ክለሳና ለሌሎችም አገራዊ እቅዶች ግብዓት ስለሚሆን በተቀናጀ አግባብ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በሌላ በኩል የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) የመዳረሻ ጥናት (Tracer Study) የአካዳሚክ ዋና ስራ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም የ2016 ተመራቂዎች የመዳረሻ ጥናት በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ድረስ ወጥ በሆነ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መካሄድ እንዳለበትም ዶክተር ኤባ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተሮች የተገኙ ሲሆን መዳረሻ ጥናትን በሚመለከት ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Oct 31, 2025 85
የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትምህርት ዘርፉን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ያነሷቸውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ፦

👉🏾ትምህርት ላይ ዋናው ሥራ ቅደመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው።
👉🏾በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ክ43 ሚሊየን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መጽሃፍትን በማሳተም ለተማሪዎች አንድ ለአንድ ማድረስ ተችሏል።
👉🏾ለመምህራን ጥራት ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠና በማዘጋጀት በየደረጃው እየተሰጠ ይገኛል።
👉🏾የትምህርት ቤት መገባ ፕሮግራም ወላጆች ሳይጨነቁ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ በእጅጉ አግዟል።
👉🏾በትምህርት ለትውልድ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት ማሻሻል ህዝባዊ ንቅናቄ ትምህርት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብረው አስደናቂ ተግባር እየፈጸሙ ነው።
👉🏾መንግስት እያካሄደ ያለው የኮሪደር ልማት በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን በማስወገድ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጻኦ አበርክቷል፣
👉🏾ልጆቻችን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረግን የምንመኛትን ኢትዮጵያ መፍጠር አንችልም በማለት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Oct 28, 2025 80

ሚኒስትሮቻችን

MINISTER

ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር

STATE MINISTER

ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ

አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ

STATE MINISTER

ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ

ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ

STATE MINISTER

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት

የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ

የተቋሙ አደረጃጀት

ይህ ዋናው የትምህርት ሚኒስቴር አወቃቀር ሰንጠረዥ ነው

አጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ

የሥርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የቋንቋና ተጓዳኝ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

የማህበራዊ ሣይንስ ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

የሥራና የተግባር ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ

የትምህርት ቋንቋዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ

የሒሳብ፣ ሳይንስና ሥነ ጥበብ መምህራን ማበልፀጊያ ዴስክ ኃላፊ

የትምህርት ኘሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የመደበኛ ትምህርት ኘሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ

የአርብቶ አደርና ልዩ ፍላጐት ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

የትምህርት መሠረተ ልማትና አገልግሎቶች ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ

የጐልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የጐልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

መደበኛ ያልሆነና የሕይወት ዘመን ትምህርት ኘሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ

ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ

የጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ

የሥርዓተ-ትምህርትና ኘሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ

የመምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ

የምርምርና ስርጸት ዴስክ ኃላፊ

የምርምር ስነ-ምግባር ዴስክ ኃላፊ

የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ኃላፊ

የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል እውቀት ዴስክ ኃላፊ

የአስተዳደር እና መሰረተ-ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ

የአስተዳደር ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ

የተቋማት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ

የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዴስክ ኃላፊ

የስኮላርሽፕና አለማቀፋዊነት ዴስክ ኃላፊ

አይቲና ዲጂታል ትምህርት መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የስኩልኔት አይሲቲ ዴስክ ኃላፊ

የትምህርት የመልቲ ሚዲያ ፕሮግራም ዝግጅት ዴስክ ኃላፊ

የትምህርት ሚዲያሰተትዱዮ ኦፕሬሽንና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ

የኔትዎርክ ቴክኒካል ዴስክ ኃላፊ

ኔተዎርክ ኦፕሬሽን ዴስክ ኃላፊ