News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Oct 09, 2020 465 views

የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) ከእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮኔስ ሃግ ጋር በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ በበየነ መረብ መክረዋል።

የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ በገጠር አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና በስደተኝነት የሚኖሩ ህፃናት ትምህርት እንዲያገኙ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የተማሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት የመላክ ልምድ አላቸው ብለን እናምናለን ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ) የጎልማሶች ትምህርት በአዲስ ስልት ለመስጠት እንቅስቃሴ መጀመሩን አብራርተዋል።

መደበኛ ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በሚገባ እንዲረዱት 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ላይ ልዩ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት እንደሚሰጥ ገለፀው የእንግሊዝ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ባሮኔስ ሃግም መንግስታቸው ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ትምህርት መስክ የምትሰራቸው ስራዎችን ይደግፋል ብለዋል።

የእንግሊዝ መንግስት የትምህርት ዘርፉን ከሚደግፉ ሀገራት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን ለዚህ ድጋፉ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Recent News
Follow Us