News Detail
Jun 30, 2025
52 views
የትምህርት ሚኒስትሩ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀመሩ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ከሾጌ የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተናን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው አስጀምረዋል።
በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንክሮ ያጠና ተማሪ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችል በማንሳት ተማሪዎች ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አበረታተዋል።
የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በዛሬው እለት በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።
ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሃምሌ 08/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል