News Detail
Oct 19, 2021
311 views
የትምህርት ሚኒስትሩ ከሰራተኞች ጋር በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ከትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ ሰራተኛ ጋር በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ በሚገቡ ጉዳዬች ላይ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም ሰራተኛው በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ አሉ ያሉትን የአሰራር ፣ የመልካም አስተዳደር እና የአደረጃጀት ችግሮች ለሚኒስትሩ ገልፀዋል።
በቀጣይም ሚኒስትሩ በተቋም ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመፈተሽ መፍትሄ የመስጠት እና የትምህርት ሴክተሩን ከ ፓለቲካ እና ከ ንግድ ነፃ ለማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ ሰራተኞቹ ገልፀዋል።
ሚኒስትሩም በሰራተኞች የተነሱትን ሀሳቦች እንደ ግብዓት በመውሰድ እና መፍትሄ በመስጠት በቅንጅት የተሻለ ስራዎችን ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የትምህርት ሴክተሩ የፓለቲካ መስሪያ ቤት ሳይሆን ህዝብን ለማገልገል የተቋቋመ ሴክተር በመሆኑ የፓሊቲካ አመለካከታችንን ትተን ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በቀጣይም ሚኒስትሪው የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ተቋም በመሆኑ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚጠበቅም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
Recent News
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
Dec 09, 2024
የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።
Dec 07, 2024