News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Feb 23, 2021 283 views

የትምህርት ብርሃን ምዘና ፈተና ከመጋቢት 15 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡

የትምህርት ብርሃን ምዘና ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመጋቢት 15,2013 ዓ.ም ጀምሮ ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ምዘናው በሚሰጥበት ሁኔታ ላይ ከየክልሉ ከተውጣጡ የጎላማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ምክክር እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱም ሀገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን ምዘናው መጋቢት 15,2013ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ይፋ ከተደረገ በኋላ በሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

 የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ  ጌታሁን ጋረደው(ዶ/ር) ምዘናው እንደ ሀገር የተማረ የሰው ሃይልን ለመለየት የሚያስችል  መሆኑንና  በተለያየ መንገድ ተምረው ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የሚችሉ ጎልማሶች ሁሉ በምዘናው እንዲያልፉ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

የምዘና ፈተናው ጎልማሶቹ ማንበብ መፃፍና ማስላት በሚችሉበት ቋንቋ የሚዘጋጅ መሆኑም ነው የተነገረው።

በምዘናው 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ከ3ኛ ክፍል ወደ 4ኛ ክፍል መዘዋወራቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት እንደሚሰጥም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በተለያየ መንገድ ፣በሀይማኖት ተቋማትየተማሩ፣በመሰረ-ትምህርት የተማሩ እንዲሁም ሀገር በቀል እውቀት ያገኙ  በምዘናው  እንደሚካተቱ ተገልጿል።

ምዘናው የተሳካ እንዲሆንና የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ስኬታማነት  ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

Recent News
Follow Us