ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ

ዋና ስራ አስፈጻሚ

ዶ/ር ሰለሞን ቢኖር

ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ

የምርምርና ስርጸት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

ዶ/ር ሰራዊት ሀንዲሶ

የምርምርና ስርጸት ዴስክ ኃላፊ


      • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምርምር ጥራ፣ ተገቢነት እና ስርፀትን የሚያሳድግ 
        የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ እና እንዲጠናከር ማድረግ፡፡
    •  
      • የሀገር ውስጥ ምርምር ጆርናሎች ፍተኛና እውቅና ስርዓት በመዘርጋት ጥራትና 
        እይታቸው እንዲጨምር ማድረግ፡፡
    •  
      • የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን የምርምር ስፋትና አቅምን ማሳደግ
    •  
      • የክትትልና ድጋፍ ድጋፍ ስራዎችን መስራት

የምርምር ስነ-ምግባር ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

ዶ/ር አቡሌ ታከለ

የምርምር ስነ-ምግባር ዴስክ ኃላፊ


የምርምር ስነ-ምግባር ዴስክ/ ስክሬታሪያት ሃላፊነት የሚከተሉት ናቸው::

  • የምርምር ፕሮቶኮል ማመልከቻዎችን ከተቋማዊ የምርምር ስነ-ምግባር ገምጋሚ ኮሚቴ/ ተማራማሪዎች በመቀበልና በብሔራዊ የምርምር ስነ-ምግባር ገምጋሚ ቦርድ በማስገምገም የምርምር  ስነ-ምግባር ፍቃድ መስጠት።
  • የቦርዱን መደበኛ እና ኢመደበኛ ስብሰባዎችን ማመቻቸት ማስኬድ።
  • የቦርዱን ውሳኔዎች ለተመራማሪዎች እና አመልካች ተቋማት  ማሳወቅ።
  • ሁሉንም የቦርድ ፕሮቶኮሎች፣ የደብዳቤ ልውውጦች፣ ውሳኔዎች እና ቃለ ጉባኤዎች አደራጅቶ ማያዝ።
  • ከየተቋማት የሚመጡ ግማሽ አመት እና አመታዊ ሪፖርቶችን መቀበልና በምርምር ስነ-ምግባር ላይ ኮንፈረንሶችን ማካሄድ።
  • በምርምር ስነ-ምግባር ቴክኒካል መመሪያና የአሰራር ስርአት መሰረት የተቋማት ምርምር ስነ-ምግባር ገምጋሚ ሚቴዎችን ምስገባ ማካሄድ፣ ድጋፍና ክትል ማድረግ።
  • በቦርዱ እና በሌሎች የተቋማት የምርምር ስነ-ምግባር ኮሚቴዎች መካካል ያለውን ትስስር መደገፍና ማጠንከር። 
  • የጥናትና ምርምር ስነ-ምግባራዊ አተገባበርን የክትትልና ግምገማን ማመቻቸት እና ማካሄድ።
  • የጥናትና ምርምር ስነ-ምግባር ስልጠና ፕሮግራሞችን ማደራጀት፣ መደገፍ፣ማመቻቸትና መስጠት።
  • የብሔራዊ የምርምር ስነ-ምግባር ቦርድ ድጋፍና ክትትል ተግባራትን በብቃት ለማድረስ ተጨማሪ በጀቶችን የማፈላለግ  ስራ መስራት 
  • የተመዘገቡትን በተቋማት የምርምር ስነ ምግባር ገምጋሚ ኮሚቴ ቁጥጥር ስር ያሉትን ሁሉንም የተከናወኑ እና የተጠናቀቁ ምርምሮችን የመረጃ ቋት ማደራጀት መመዝገብ እና መያዝ።

የብሔራዊ የምርምር ስነ ምግባር ቦር

የቦርዱ ዋና ሚና በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሚቀርቡ የምርምር ፕሮቶኮሎችን በመገምገም እና የምርምር ስነ ምግባር ፍቃድ በመስጥት  እና ክትትል በማድረግ የምርምር ተሳታፊዎች እና/ ወይም የማህበረሰቡ  ክብር፣ መብት፣ ጥቅም እንድህንት እንዲጠበቅ ማስቻል ነው

የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

አቶ ተሾመ ዳንኤል

የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ኃላፊ


      • የስራ ክፍሉ ዋና ዋና ተግባራት እና ኃላፊነቶች የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ ምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ስራዎች ማለትም ለጋራ ተግባራዊ ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ለኢንተርንሽፕ፣ ለኤክስተርንሽፕ፣ ለትብብር ሥልጠና እና ለማማከር አገልግሎት ስራዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ነው።  

         አስቻይ የህግ ማዕቀፎችን ከማውጣት እና የተቋማት ኢንዱስትሪ ትስስር ተግባራትን ከማስተባበር በተጨማሪ የቴክኖሎጂ እና የምርምር ውጤቶች ወደ ገባያ የማስገባት እና ለተጠቃሚው ተደራሽ የሚደረጉበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት፣ የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማሳደግ እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር እንዲኖር የበኩሉን ሚና የመጫወት ድረሻ አለው።

        የስራ ክፍሉ በትስስር አዋጅ 1298/15 መሰረት በአገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ትስስር ምክር ቤት ሴክሬታሪያት ሆኖ የማንቀሳቀስ እና የአካዳሚያዊ ኢንዱስትሪ አጋርነትን የማመቻቸት ሚናዎች እና ኃላፊነቶች አሉት።

የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል እውቀት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

ወ/ሮ ሰላም አለሙ

የማህበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል እውቀት ዴስክ ኃላፊ


      • የማሕበረሰብ ጉድኝትና ሀገር በቀል ዕውቀት ዴስክ ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት ሥራው የሚከናወነው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኩል በመሆኑ ከተቋማቱ ጋር ጥብቅ የሆነ ትስስር በመፍጠር ተቀናጅቶ መስራትየሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
    •  
      • በሥሩ የሚከናወኑትን የተለያዩ ተግባራቶች በተመለከተ ለባለሙያዎች ማለትም ለማህበረሰብ ጉድኝት ፣ ለሂሳብ ሳይንስና ቴክኖሎጂ  እና ለሀገር በቀል ዕውቀት ልማት ባለሙያዎች  ፣  በተሰጣቸው የሥራ ዝርዝር እና በተቋሙ ዕቅድ መሰረት ሥራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
    •  
      • የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠት፣ ሪፖርት ለሚመለከተው አካል ማድረስ፣ ከተለያዩ ክፍሎች ለዴስኩ የሚመጡ ደብዳቤዎችን በተመለከተ ውሳኔ በመስጠት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ
    •  
      • የሥራ ክፍሉን እንቅስቃሴ በተመለከተ ከተቋሙ የበላይ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረግ
    •  
      • በየተቋማቱ የሥራ ክፍሉን ሥራ ማሳለጥ የሚያስችሉ ማዕከላት የሚቋቋሙበትን መንገድ ማመቻቸት
    •  
      • ተቋማቱ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የፋይናስ ድጋፍ የሚያገኙበትን  መንገድ ማመቻቸት።