ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ

ዋና ስራ አስፈጻሚ

ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ

ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ

የአስተዳደር እና መሰረተ-ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ

የአስተዳደር ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

አቶ አብዶናስር ሃጂ

የአስተዳደር ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ


      • የመምህራንና ተማሪዎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች
    •  
      • የተማሪዎች ምደባ
    •  
      • የወጪ መጋራት አገልግሎት
    •  
      • የአስተዳደር ሠራተኞችና በጤና ባለሙያዎች አገልግሎት አሰጣጥ አስተዳደራዊ ጉዳዮች፡፡

የተቋማት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

አቶ ጫኔ አደፍርስ

የተቋማት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ


      • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር ልማትና አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት፣ የተቋማትን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማጎልበት፣
    •  
      • የከፍተኛ ትምህርት አመራሮችን የስልጠና ፍላጎት በመለየት፣የሚሰለጥኑበትን ስርአተ ትምህርት በማዘጋጀት፣ በመከለስ፣ የስልጠና ሞጁሎችን በማዘጋጀት፣ ስልጠና በመስጠት፤ የስልጠናዎቹን ፋይዳ በመገምገም፣ በተቋማት የአመራር ልማትና  አስተዳደር ሥርዓት ላይ በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ጥናትና ምርምር በማካሄድ
    •  
      • በተጨማሪም አዋጭ የሆኑ ፕሮፖዛሎችን በመቅረፅ እና ሃብት በማፈላለግ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የአመራሮችን መረጃ በመሰብሰብ እና በመተንተን ፤በተቋማቱ በየደረጃው ያሉ አመራሮችን በመመዘን፣የአፈጻጸም ደረጃቸውን በማውጣትና ወቅታዊ ግብረ መልስ ፣ የአመራር ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች  አቅም ግንባታ አፈፃጻም ላይ ድጋፍና ክትትል ግምገማ በማድረግ፤ በአመራር አቅም ግንባታና አደረጃጀቶች ላይ መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት፣ በመቀመርና በማስፋት፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና የተገልጋዩ ማህበረሰብ አገልግሎት እርካታና አመኔታ እንዲረጋገጥ በማድረግ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመማር ማስተማር፤ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ተልዕኳቸ ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲፈፅሙ ማድረግ ነው፡፡

የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

አቶ ዘውዱ ካሳ

የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዴስክ ኃላፊ


      •  ለመሠረተ ልማት፣ለምደረ-ግቢ፣ለአይሲቲ፣ለሳይንስ መሣሪያዎች እና ለትምህርት ፕሮግራሞች ስታንዳርዶችንና የትግበራ ማኑዋሎችን አዘጋጅቶ በመተግበር ለመማር ማስተማር ሥርዓቱ ምቹ ሁኔታን መፍጠር
    •  
      • ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የልዕቀት እና ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከላትን በማቋቋም የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሳደግ 

የስኮላርሽፕና አለማቀፋዊነት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

ዶ/ር ኤዶሳ ተርፋሳ

የስኮላርሽፕና አለማቀፋዊነት ዴስክ ኃላፊ


  •   የስራ ክፍሉ የከፍተኛ ትምህርት  አለማቀፋዊነት እና የስኮላርሺፕ  ጉዳዮችና ተግባራትን የመከታተል፣የመደገፍ፣የማስተዳደር እና የማስተባበር ተግባርና ሃላፊነት  ተጥሎበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከሀገራትና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር የሚደረጉ የሁለትዮሽና ባለ ብዙ ጎን የትብብርና አጋርነት ስራዎች  የመቅረጽ፣የመደገፍ፣የመከታተል፣የማበልጸግ፣የመፈጸምና ሃላፊነት ተጥሎበታል፡፡