አጠቃላይ ትምህርት
ዋና ስራ አስፈጻሚ
አቶ ዮሃንስ ወጋሶ
አጠቃላይ ትምህርት
የትምህርት ኘሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ ሥራ አስፈፃሚ
የመደበኛ ትምህርት ኘሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ
ዴስክ
አቶ ታዬ ግርማ
የመደበኛ ትምህርት ኘሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ
-
-
- በመማር ማስተማሩ ሂደት አቅም እየጎለበተ መሄዱን በመገምገም የማሻሻያ የፖሊሲ ሃሰብ ያቀርባል፣ በተሻሻለው መሰራት ተግባራዊ እንዲሆን አመራር ይሰጣል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
-
- የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት አተገባበር ለመገምገም የሚያስችል የመገምገሚያ መስፈርቶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ ያጸድቃል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
-
- በትምህርት ቤት ደረጃ የሚሰጡ የምዘና ሂደቶች በተገቢው እና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ስልት ይቀይሳል፣ እንዲተገበር አመራር ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
-
- በትምህርት ፕሮግራሞችና ጥናት አተገባባር ዙሪያ የስልጠና ሰነዶች ያዘጋጃል ስልጠና ይሰጣል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ያስገኙትን ፋይዳ ይለያል፡፡
-
- የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በተፋጠነ መንገድ ማሻሻል (Accelerated School Transformation) የሚቻልባቸውን ስልቶች በመዘርጋት ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አመራር ይሰጣል፣ ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ ሪፖርት ያዘጋጃል፣
-
- ለተማሪዎች የትምህርት ውጤት ከፍተኛ መሆን አስተዋፅዖ የሚያደርጉትን የትኩረት ጉዳዮች (Focus Areas) ይለያል፣ እንዲተገበር አመራር ይሰጣል፡፡
-
- የትምህርት ቤት ፋሲሊቲንና ግብዓቶችን ማሰራጨት የሚያስችል የትምህርት ቤቶችን አቀማመጥ ስርጭት ካርታ (School Mapping) እንዲዘጋጅ አመራር ይሰጣል፣ ተግባራዊ እንዲደረግ ያደርጋል፤ያረጋግጣል፡፡
-
የአርብቶ አደርና ልዩ ፍላጐት ትምህርት ዴስክ ኃላፊ
ዴስክ
ወ/ሮ መሠረት በቀለ
የአርብቶ አደርና ልዩ ፍላጐት ትምህርት ዴስክ ኃላፊ
ልዩ ፍላጎት፣ የአካል ጉዳተኛ እና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከትምህርት ዘርፍ ልማት በፍትሀዊነት ተጠቃሚ መሆን የሚያስችሉ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ፓኬጆችን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ትግበራውን ይደግፋል፤ ይከታተላል፤ አፈጻጸሙን ይገመግማል፡፡
-
-
- የአርብቶ አደር እና ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከትምህርት ዘርፍ ልማት በፍትሀዊነት ተጠቃሚ መሆን የሚያስችሉ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ፓኬጆችን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ትግበራውን ይደግፋል፤ ይከታተላል፤ አፈጻጸሙን ይገመግማል፡፡
-
- ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች በትምህርት ልማት ዘርፍ የሚታዩትን የአፈጻጸም ክፍተቶች በመለየትና አገራዊ ግብን መሰረት በማድረግ በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት አመራርና ባለሙያዎች አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ የሥልጠና ማንዋሎችን በማዘጋጀት ሥልጠና ይሰጣል፤ ያመቻቻል፤ ያስተባበራል፡፡
-
- በልዩ ፍላጎት/አካቶ /ትምህርት ስራዎች ላይ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ፕሮግራም መሳካት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ያስተባብራል፤ ይከታተላል፤ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
-
- ለአርብቶ አደር፣ ለልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማግኘት የሚረዳ የፕሮጄክት ሀሳብ ያመነጫል፣ ባለሙያዎችን በማስተባበር ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
-
- በፌደራል የመንግስት አስፈጻሚ አካላት አዋጅ እና በልዩ ድጋፍ ቦርድ ማቋቋሚያ ደንብ መሰረት የተሰጡ ተግባርና ኃላፊነቶችን በተቀናጀ ድጋፍ ለመፈጸም የሚያስችል እቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ እቅዱን ያጸድቃል፡፡
-
- የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ውስንነት በሚታይባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ የአጠቃላይ ትምህርት መዋቅሮች ልዩ የሆነ የሱፐርቪዥን ድጋፍ እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ያሰራል፤ ይከታተላል፤ ጥናት ላይ በመመሥራት እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡
-
የትምህርት መሠረተ ልማትና አገልግሎቶች ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ
ዴስክ
አቶ ዳዊት አዘነ
የትምህርት መሠረተ ልማትና አገልግሎቶች ጉዳዮች ዴስክ ኃላፊ
-
-
- በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ስር ያሉ የትምህርት ተቋማት በጥራት ለሁሉም ዜጐች ተደራሽ ሆነው እንዲስፋፉ የሚያስችሉ የግንባታ መሰረተ ልማቶችን ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ ክልሎች ሙያዊ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ጥናት ላይ በመመሥራት እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡
-
- በህብረተሰብ ተሳትፎ እና በአጋር የልማት አካላት ለሚገነቡ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ተቋማት የግንባታ መሰረተ ልማቶችን በሀገራዊ ስታንዳርድ መሰረት እንዲሆን ሙያዊ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ይከታተላል፡፡
-
- ትምህርት ቤቶች ለሁሉም ተማሪዎች ምቹ እና ለደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ የመብራት፣ የንፁህ መጠጥ ውሀ፣ የመፀዳጃ፣ የአጥር፣ ከአደጋ ነጻ ከባባዊ ሁኔታ ወዘተ ለማድረግ የሚያስችሉ ፋሲሊቲዎች እንዲኖሩ የሚያስችል የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ይከታተላል፡፡
-
- በትምህርት ኢንስፔክሽ ደረጃ ፍረጃ ውጤት መሰረት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ከግንባታ መሰረተ ልማቶች ጋር የተያያዙ ክፍተቶችን በመለየት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ሙያዊ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤ ይከታተላል፡፡
-
- ከትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እና ሌሎች የአገልግሎት አቅርቦቶች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ለሚሰጡ ውሳኔዎች የሚረዳ የመረጃ ትንተና (Data analysis) እና ነባራዊ ሁኔታ (trend analysis) እንዲሰራ በማድረግ ገምግሞ ለውሳኔ ሰጪዎች ያቀርባል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
-
- በየትምህርት ቤቱ ከምገባ ጋር በተያያዘ በጤና ጉዳዮች ላይ የሚነሱ የፋሲሊቲና የአቅርቦት ሁኔታዎች ክትትል በማድረግ አቅርቦት የሚሻሻልበትን ስልት እንዲቀየስ ባለሙያዎችን ያስተባብራል፤ የውሳኔ አሰጣጥ አማራጭ ስልቶች ቀምሮ ያፀድቃል፤ ሲወሰንም ትግበራውን ይከታተላል፡፡
-
- የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም የሎጂስቲክስና ግዥ አገልግሎት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና ከትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ጋር በተያያዥነት የሚሰራበትን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ መመሪያ ያዘጋጃል፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፡፡
-
- በትምህርት ቤቶች የግንባታ መሰረተ ልማቶች፣ የአገልግሎት አቅርቦቶች እና ግብዓቶች ዙሪያ በትምህርት ማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ የግንዛቤ፣ የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመለየት የዳሰሳ ጥናት በማድረግ ፍላጎቶችን በቅደም ተከተል ይለያል፤ የሚፈቱበትን ስትራቴጂ ያዘጋጃል፤ ትግበራውን ይከታተላል፡፡
-
- በሰው ሰራሽና ተፈጥሮዊ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ተቋማት አገልግሎቶች ሲቋረጡ የግንባታ መሰረተ ልማቶች መልሰው እንዲደራጁ ድጋፍ ያደርጋል፤ አዳዲስ አማራጭ ስልቶች ሲነደፉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያስተባብራል፡፡
-
የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ
ዴስክ
አቶ በላይ አወቀ
የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዴስክ ኃላፊ
-
-
- በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚካሄደውን የኢንስፔክሽን አገልግሎት ሥራ ይመራል፣ ያስተባብራል፤
-
- የኢንስፔክሽን ማስተግበሪያ ማዕቀፎች፣ መመሪያዎችና የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን ያዘጋጃል፥
-
- የስልጠና ማኑዋልና ፓኬጅ በማዘጋጀት በየደረጃው ለሚገኙ የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች በኢንስፔክሽን ማስተግበሪያ ሰነዶች ላይ የአቅም ግንባታ የአሰልጣኞች ሥልጠና ይሰጣል፤
-
- የአፀደ ሕፃናት ፣ የኦ-ክፍል፣ የአማራጭ መሰረታዊ ትምህርት፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በትምህርት ቤት መሻሻል ስታንዳርዶቹ መሰረት የተሟላ የትምህርት አገልግሎት መስጠታቸውን በናሙና ኢንስፔክሽን ያረጋግጣል፤
-
- በየደረጃው በሚገኙ የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች ለትምህርት ቤቶች የተሰጡ የኢንስፔክን አገልግሎቶች ጥራትና ብቃት በመከታተልና በመገምገም ግብረ-መልስ ይሰጣል፣
-
- የትምህርት ስታንዳርድ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጠበቁን የሚያረጋግጡ መረጃዎችን ያሰባስባል፤ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ ዓመታዊ እና የሦስት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለባለድርሻ አካላት ያቀርባል፣ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል፣ ለውሳኔ ሰጪ አካላት አቅርቦ ያፀድቃል፣ ስራ ላይ ያውላል፤
-
- ኢንስፔክሽን ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያደረገውን አስተዋፅዎ ጥናትና ምርምር በማካሄድ አሰራሩን ይፈትሻል ፣ በግኝቶቹንም ላይ የውይይት መድረክ ያዘጋጃል፣ ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ የውሳኔ ሀሳቦችን ለባለድርሻ አካላት ያቀርባል፤
-
- በኢንስፔክሽን አተገባበር ዙሪያ ምርጥ ተሞክሮ ካላቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በመቀመር ያሰፋል፥ ለሥራው በግብዓትነት ይጠቀማል፤
-
- በትምህርትቤት መሻሻል የተዘረጋው የኃላፊነትና የተጠያቂነት ሥርዓት በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤
-
- የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ የሚሰበሰቡትን የኢንስፔክሽን መረጃዎች በመረጃ መረብ ሥርዓት (Web based) እንዲታገዝ ያደርጋል፤
-
- በኢንስፔክሽን ትግበራና አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የአሕዝቦትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤
-
- በኢንስፔክሽን አፈፃፀም ሂደትና ውጤት ዙሪያ የሚቀርቡትን ቅሬታዎች ያጣራል፣ ያረጋግጣል፤ የማስተካከያ ዕርምጃም ይወስዳል፤
-