አጠቃላይ ትምህርት

ዋና ስራ አስፈጻሚ

ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ

አጠቃላይ ትምህርት

የሥርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ሥራ አስፈፃሚ

የቋንቋና ተጓዳኝ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

ዶ/ር አበበ ጋረደው

የቋንቋና ተጓዳኝ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ


          • ጥናትና ምርምር በማካሄድ ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ ማድረግ
          • ፕሮጀክት መቅረጽ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማሰፋፋት
          • የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣ ደንብ፣ መመሪዎችና ማዕቀፎችን ማዘጋጀት
          • የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ማዘጋጀትና ስልጠናውን መስጠት
          • ሥርዓተ ትምህርት ለማጋዘጀት እንዲሁም ለማሻሻል እና ለማስተግበር ቅድመ ሥራዎችን ማከናወን
          • ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት፣ ማሻሻል እና ማስተግበር
          • ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ ለማድግና ጥራቱን ለማስጠበቅ ቀጥጥር፣ ክትትል፣ ግምገማና ድጋፍ ማድረግ
          • የመማሪያ ማስተማሪያ መጻሕፍት ማዘጋጀት፣ ጥራት የማረጋገጥ ሥራን መስራት

የማህበራዊ ሣይንስ ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

አቶ ኡመር ኢማም

የማህበራዊ ሣይንስ ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ


      • የትምህርት ሚኒስቴርን አስር አመት ዕቅድ መሰረት በማድረግ የዴስኩን ስትራቴጂክ ዕቅድ፤ አመታዊ ዕቅድና ዕለታዊ የተግባር ዕቅድን ያዘጋጃል፤ በስራ ላይ ያውላል፤ ሪፖርት ያደርጋል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል።
      • ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ለውጦችን መሰረት ያደረገ፤ የሀገር በቀል እውቀትና ክህሎቶችን ያካተተ፤ በላቀ ደረጃ የፈጠራ ስራ የሚያበረታታና በቴክኖሎጂ የበለፀገ ሥርዓተ ትምህርት ያዘጋጃል፤ ያሻሽላል፤ ይተገብራል፤ ይገመግማል፤ ይለውጣል፡፡
    •  
      • የሁለተኛ ደረጃ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች የትምህርት ዓይነት አቋም መግለጫ፤ መርሃትምህርት፤ የይዘትፍሰቶች፤ የመማርብቃቶች፤ የየእርከኑ የተማሪ ፕሮፋይል በማዘጋጀት የመማሪያ ማስተማሪያ መፃህፍት በጥራት በማዘጋጀት ይተገብራል፤ ተገቢነቱንም ያረጋግጣል።
    •  
      • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተከታታይ ምዘና ከመማሪያ ማስተማሪያ መፃህፍቶች መማር ብቃቶች አኳያ መዘጋጀታቸውን ይከታተላል፤ ያስተባብራል፤  ይመራል፡፡ 
    •  
      • ለቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ ደረጃና መካከለኛ ደረጃ የየትምህርት ዓይነት አቋም መግለጫ፤ መርሃ ትምህርት፤ የይዘት ፍሰቶች፤ መማር ብቃቶች፤ የየእርከኑ የተማሪ ፕሮፋይል መሰረት ጥራት ጠብቆ መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፡፡
    •  
      • ለዴስኩ ስራ ማስኬጃ የበጀት ምክረ ሀሳብ ያዘጋጃል፤ ያፀድቃል፤ በመመሪያ መሰረት ለታለመለት ዓላማ ያውላል፤ በስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤ ግብረ-መልስ ይሰጣል፤ የበጀት ሪፖርት ያዘጋጃል፤ ለበላይ አካል ያቀርባል፡፡
    •  
      • በስርዓተ ትምህርት አተገባበር ዙሪያ ላይ ለሚገጥሙ ችግሮች የምርምር ርዕስ ይለያል፤ ጥናትና ምርምሮች ያካሂዳል፤ የጥናትና ምርምሮችን ውጤቶች መሰረት ያደረገ ምክረ-ሀሳብ ለመሪ ስራ አስፈፃሚ ያቀርባል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ያስተባብራል፡፡
    •  
      • የጥናትና ምርምር ውጤቶችን መሰረት በማድረግ ቁልፍ የስርዓተ ትምህርት ችግሮችን ለመፍታት ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሀብት ያፈላልጋል፤ ስትራቴጂ ይቀርፃል፤ የተገኘውን ሀብት በስራ ላይ ያውላል፤ ግብረመልስ ለበላይ አመራር ያቀርባል፡፡
    •  
      •  በዴስኩ የሚዘጋጁ ስርዓተ ትምህርት ቁልፍ ችግሮች ላይ ችግር ፈቺ ምርምር በማድረግ ሀገራዊ ሲምፖዚየምና ሴሚናር በማዘጋጀት ምርጥ ተሞክሮ የመለየት፤ የመቀየርእና የማስፋት ስራ ያከናውናል፡፡
    •  
      • የሥርዓተ ትምህርት ደንቦች፤ ስትራቴጂዎች፤ ስታንዳርዶች፤ መመሪያዎችና ማኑዋሎች ሲዘጋጁና ሲሻሻሉ ምክረ-ሀሳብ ያመነጫል፤ ስልት ይቀይሳል፤ ግብረ-መልስ ይሰጣል፤ ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤ ይገመግማል፡፡
    •  
      •  የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት፤ የይዘት ለውጦችና የመማር-ማስተማርስነ-ዘዴዎችን አተገባበር በተመለከተ ስልቶችን ይዘረጋል፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፤ ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይከታተላል፤ ይገመግማል፡፡
    •  
      •  የሥርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ ዝግጅት፤ መማሪያ ማስተማሪያ ማቴሪያሎች፤ ሀገራዊ ትኩረት የሚሹና ድንበር ተሸጋሪ ጉዳዩች ላይ ሙያዊ አሰራርን ተከትሎ ሥርዓተ ትምህርት ያዘጋጃል፤ ያስተባብራል፤ ይመራል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡፡
    •  
      •  የሥርዓተ ትምህርት ስታንዳርዶችና የብቃት መለኪያዎችን ውጤታማነት ከአገራዊ ፋይዳ አኳያ ይገመግማል፤  ክትትልና ድጋፍያደርጋል፡፡
    •  
      • የሥርዓተ ትምህርት አተገባበር ላይ ሂደታዊ እና አጠቃላይ ግምገማ እንዲካሔድ ያስተባብራል፤ ይከታተላል፤ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

ዛፉ አብርሃ

የተፈጥሮ ሣይንስ ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ


      •      ለተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ማዘጋጀት፣ ማስተግበርና ግምገማ ማካሄድ እና ማሻሻል
      • የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት አተገባበርና ጥራት ለማስጠበቅ የቁጥጥር፣ ክትትልና ግምገማ ማካሄድ።
      • ለሁለተኛ ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት የመማሪያ ማስተማሪያ መጽሐፍት ማዘጋጀት፣ እንዲታተሙና እንዲሰራጩ ማድረግ
      •    የአካቶ ሥርዓተ ትምህርት አተገባበርን መከታተል፣ መገምገምና ማሻሻል
      •  የስራ ክፍሉን እቀድ ማዘጋጀት፣ መተግበርና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማቅረብ
      • ጥናትና ምርምር ማካሄድ ስርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ እንዲሆን ጥረት ማድረግ
      • ፕሮጅክት መቅረጽ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት
      • የአሰራር ሥርዓተ መዘርጋት፣ ደንብና መመሪያዎች፣ ማዕቀፎችን ማዘጋጀት
      •  የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀትና ስልጠናውን መሰጠት
      • ለክልሎች በሥርዓተ ትምህርት አተገባበር ላይ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ
      • የትምህርት ፖሊሲ ሃሳቦችን ማመንጨት፣ ማዳበርና ለሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ግብዓት መስጠት
      • ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ትኩረት ስጥቶ መስራት

 

የሥራና የተግባር ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ

ዴስክ

አቶ ማተቤ አለማየሁ

የሥራና የተግባር ትምህርቶች የሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ


ሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ዋናው ዓላማ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ ሥራ ፈጥረው ወይም ተቀጥረው እንዲሰሩ እና ለቀጣይ ትምህርት ማዘጋጀት ነው። ከላይ የተጠቀሰውን ዓላማ ለማሳካት የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ዋና ዋና ተግባር እና ኃላፊነት የሚከተሉት ናቸው።

      • ሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ዋናው ዓላማ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ ሥራ ፈጥረው ወይም ተቀጥረው እንዲሰሩ እና ለቀጣይ ትምህርት ማዘጋጀት ነው።
      • ከላይ የተጠቀሰውን ዓላማ ለማሳካት የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዴስክ ዋና ዋና ተግባር እና ኃላፊነት የሚከተሉት ናቸው።
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ሰነዶች የሆኑትን የሥርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ፣ የሙያ ደረጃ፣ የብቃት ፍሰት፣ የይዘት ፍሰት፣ መርሐ ትምህርት፣ የመማሪ ማስተማሪያ እና ማሰልጠኛ ሰነዶች እንዲሁም ደጋፊ ሰነዶችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ያሻሽላል፤ መተግበራቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል። የተዘጋጁትን ሰነዶች ያሳትማል፣ ያሰራጫል።
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርትን ለመምህራን፣ ለትምህርት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ያስተዋውቃል።
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ደንቦች፣ ስትራቴጂዎች፤ ስታንዳርዶች፤ መመሪያዎችና የሥራ ማንዋሎች ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ያሻሽላል፤ መተግበራቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል። የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይቀምራል፤ ያስፋፋል።
      • ሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ የወጡ ፖሊሲ፣ ደንቦች፣ ስትራቴጂዎች፤ ስታንዳርዶች፤ መመሪያዎችና የሥራ ማንዋሎች ላይ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል።
      •  የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ ትግበራ እና ግምገማ ጥናትና ምርምር ያከናውናል። የጥናት ውጤት ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች ሥርዓተ ትምህርቱን ለማሻሻል በግብዓትነት ይጠቀማል
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግና ጥራቱን ለማስጠበቅ ቁጥጥር፤ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል።
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ሰነዶች የሆኑትን የሥርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ፣ የሙያ ደረጃ፣ የብቃት ፍሰት፣ የይዘት ፍሰት፣ መርሐ ትምህርት፣ የመማሪ ማስተማሪያ እና ማሰልጠኛ ሰነዶች እንዲሁም ደጋፊ ሰነዶችን ያዘጋጃል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ያሻሽላል፤ መተግበራቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል። የተዘጋጁትን ሰነዶች ያሳትማል፣ ያሰራጫል።
      •  የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርትን ለመምህራን፣ ለትምህርት አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት ያስተዋውቃል።
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ደንቦች፣ ስትራቴጂዎች፤ ስታንዳርዶች፤ መመሪያዎችና የሥራ ማንዋሎች ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ያሻሽላል፤ መተግበራቸውን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል። የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይቀምራል፤ ያስፋፋል።
      • ሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ የወጡ ፖሊሲ፣ ደንቦች፣ ስትራቴጂዎች፤ ስታንዳርዶች፤ መመሪያዎችና የሥራ ማንዋሎች ላይ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል።
      •   የሥራና የተግባር ትምህርቶች ሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ ትግበራ እና ግምገማ ጥናትና ምርምር ያከናውናል። የጥናት ውጤት ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች ሥርዓተ ትምህርቱን ለማሻሻል በግብዓትነት ይጠቀማል።
      • የሥራና የተግባር ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግና ጥራቱን ለማስጠበቅ ቁጥጥር፤ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል።