News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jan 17, 2026 70 views

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በተገነባ የት/ቤት ምርቃት ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት

በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ ሥነሥርዓት ላይ ስንገኝ በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ ይሰማናል።
ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን ያገለግላል።
ግቢው ማደሪያ ክፍሎችን፣ መማሪያ ክፍሎችን፣ በፀሃይ ኃይል የሚሰሩ በቂ ኮምፒውተሮች ያሉት የኮምፒውተር ላብራቶሪ፣ የንፁህ ውሃ ጉድጓድ፣ የተሟላ የምግብ ማብሰያ ክፍል፣ ቤተ መፃሕፍት እና የአስተዳደር ሕንፃን አካትቶ የተገነባ ነው።
ይኽ ምሉዕነት ያለው የትምህርት ከባቢ የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ልህቀት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተሰራ፣ ለወጣት ተማሪ ልጆቻችን ሁሉን አቀፍ እድገት አዲስ እድል የፈጠረ ተቋም ነው።
Recent News
Follow Us