News Detail

የሀገር ውስጥ ዜና
Jan 14, 2025 5 views

የትምህርት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባስደርን በጽ/ ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ጋር ተወያይተዋል።
በዚሁ ወቅት ትምህርት ሚኒስቴር ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በአጠቃላይና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች እየተተገበሩ ያሉ የለውጥ እርምጃዎችንና የትኩረት አቅጣጫዎችን ለአምባሰደሯ አብራርተዋል።
በተለይም ጥራት ያለው ፍትሃዊ ትምህርት ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ፣ የትምህርት ቤት ምገባ፣ የቅድመ ልጅነት ትምህርት፣ የመምህራንን የማስተማር አቅም ማሳደግ፣ የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ማሻሻል እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ራስ ገዝ ማድረግ የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።
አክለውም በትምህርት ዘርፉ ድጋፍ የሚያደርጉ አጋር አካላት የቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸውና የተማሪዎችን እኩል የመማር መብት የሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ መሆን እንዳለበት ገልጸው ለዚህም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመወያየት በጋራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገርን በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ እየስራቸው ላሉ ስራዎች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገላጸዋል።
ሁለቱ አካላት በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት እየተወሰዱ ያሉ የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ጉዳይ ላይም ሰፊ ውይይት አድረገዋል።
Recent News
Follow Us