ዜና

የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ብቃት ያለውና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተጠቆመ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር በመውጫ ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ አውደ ጥናት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በአውደጥናቱ  ላይ የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር ) በቀጣይ በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡ  የመውጫ ፈተናዎች ተገቢውን እውቀት  ክህሎትና ሰብዕና ያሟላ ምሩቅ ለማፍራት  እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

መውጫ ፈተናው በምሩቃን ፕሮፋይል መሰረት  ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃንን በማውጣት  ጥራት ያለውና በአግባቡ የሰለጠነ የሰው ሀይል ለገበያው ለማቅረብ እንደሚያስችልም ተናግረዋል፡፡

የመውጫ ፈተናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አቅማቸው እስኪጎለብትና አካዳሚክ  እና ተቋማዊ ነጻነታቸው  ሙለ በሙሉ  እስኪረጋገጥ ድረሰም ፈተናው በጊዜየዊነት በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ  ተገልጿል።