የጐልማሶችና ተከታታይ ትምህርት ዘርፍ
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ
- ዘርፉ የተቋቋመለት አላማ፤
በአገራችን ኢትዮጵያ ወጣቶችና ጎልማሶች በማሕበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማድረግ፤ ጥራትና ተገቢነት ያለው የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ኘሮግራሞች የሚሠጥበትን ስርዓት መዘርጋት፤ ወጣቱና ጎልማሳው የተለያየ ዓይነት የትምህርትና ሥልጠና አቅርቦት (Modality) በመጠቀም ልዩ ልዩ የክህሎት ሥልጠናዎችን በመውሰድ ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውና ሀገራቸውን በመለወጥ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ነው፡፡
- በተጨማሪም ይህ ዘርፍ በሀገራችን ያለውን የመፃፍ፣ ማንበብና ማሥላት ምጣኔ (Literacy rate) ለማሳደግና የሰብአዊ ልማት መለኪያ (Human development index) ከማሣደግ አንፃር ከፍተኛ ድርሻ ያለው ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ መንግስት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ለጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአዲስ እንዲደራጅና ወጣቱና ጎልማሳው የዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
- በዚህ መሠረት በትምህርት ዘርፍ የ10 ዓመት ዕቅድ (10 Years Plan) እና በስድስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሀ ግብር (ESDP VI) ለጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች እንዲካተቱና ወደ ትግበራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ እነሱም፡-
- የጎልማሶች ክህሎት ሥልጠናን ማሥፋፋት፤
- በጎልማሶች ክህሎት ሥልጠና የሴቶችን ተሳትፎ ማሣደግ፤
- የተከታታይ (የርቀትና የማታ) ትምህርት መርሀ-ግብሮችን ማስፋፋት፤
- የጎልማሶች ሙያ ክህሎት ትምህርትና ሥልጠናን ማስፋፋት፤
- የአማራጭ ትምህርት ፕሮግራም አቅርቦትን ማስፋፋት፤
- ጠንከራ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አደረጃጀት መፍጠር ናቸው፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን Components በቀጣይ አምስት ዓመት ትግበራ ላይ በማዋል በዘርፉ ጠንካራ የሆነ መሠረት ለመጣልና ወጣቱንና ጎልማሳውን ተጠቃሚ በማድረግ እንደ ሀገር ፈርጀ ብዙ ውጤቶችን ለማሥመዝገብ መጠነ ሰፊ ሥራዎች በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡