ትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ዘርፍ
የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ዳይሬክቶሬት ዓለማ፣ተግባርና ኃላፊነት
1. ዓለማ
- ጥራቱ የተጠበቀ ትምህርት በሀገሪቱ እንዲኖር ለማገዝ፣
- በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የተሻለ አቅም ያላቸውንና በሥነምግባር የታነፁ ባለሙያዎችን ወደ ሙያው ለመሳብና በሙያው ላይ እንዲቆዩ ለማስቻል፣
- በሙያው ላይ ያሉ ነባር መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ብቃታቸውን እያሳደጉ ይበልጥ ተወዳዳሪ እየሆኑ ሙያውን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግ፣
2. ተግባርና ኃላፈነት
- የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ማስተባበርና መምራት
-
- የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሠረት በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ስትራቴጂካዊና ዓመታዊ የሥራ እቅድና የበጀት ዕቅድ ማዘጋጀት፤ተግባራዊ ማድረግ፤
- የሰው ሃይል፣ በጀት፤ ሎጂስትክስና ልዩ ልዩ ግብአቶች እንዲሟሉና ለታለመለት ዓላማ ማዋል፤
- የስራ ክፍሉን የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፣መገምገም፣ የአፈፃፀም ክፍተቶችን በመለየት ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤ የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳትን በተመለከተ ከተገልጋዮች ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ምላሽ ይሰጣል፣
2.2. ጥናቶችን ማካሄድ፣ ስትራቴጂዎችንና ፕሮጀክቶችን መቅረጽ፣
- የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳትን ችግሮች የሚፈቱ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ የሚረዳ የጥናት ዕቅድ (Research Proposal) ማዘጋት፤ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ተከትሎ ማሄድ፤
- የጥናቱን ግኝት መሰረት በማድረግ የቀረቡ የማሻሻያና የመፍትሄ ምክረ ሃሳቦችን ስራ ላይ ማዋል፤
- የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ስራዎችን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ይቀርጻል፤ የሀብት ማፈላለግ ሥራ ማከናወን፤
2.3. የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ማዕቀፎችን፣ደንብና መመሪዎችን ማዘጋጀት፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት፤
- የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የሚያስችሉ አሰራሮችንና ስልቶችን መዘርጋት፤
- የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት አገልግሎትን በሚፈለገው ደረጃ ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችሉ የማስፈጸሚያ ማዕቀፎችን፣ ደንብና መመሪያዎችን ማዘጋጀትና ለሚመለከተው አካል አቅርቦ በማስጸደቅ መተግበር፤
- የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ስርዓትን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ምርጥ-ተሞክሮዎች የሚገኙባቸው አገሮችን እንዲሁም የአገር ውስጥ የስራ ክፍሎችን መለየት፣ ልምድ በመቅሰም የተገኘውን የተሻለ ተሞክሮ ቀምሮ ከአገራዊና ከስራ ክፍሉ ተጫባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መተግበር፤
- የሙያ ብቃት ምዘና ውጤትን መሠረት በማድረግ የክፍተት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የሙያ ብቃት ምዘና አሰጣጥ ሂደት ላይ ማሻሻያ ማድረግ፤
- የተገልጋይ እርካታ ያለበት ደረጃ በዳሰሳ ጥናት በመፈተሽ ማሻሻል፤
- ሌሎች የስራ ክፍሎች የሚያወጧቸው መመሪያዎች ከሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ማዕቀፎች፣ ደንብና መመሪያዎች ጋር መጣጣማቸውን ማረጋገጥ፤
- የመቁረጫ ነጥብ ላስመዘገቡ ተመዛኞች የሙያ ፈቃድ የምስክር ወረቀት መስጠትና ማደስ፣
2.4. የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት፤ መምራትና ማስተባበር ፤
- በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ዙሪያ በወጡ አዋጆች፣ማዕቀፎች፣ ደንብ፣ መመሪያዎች፣ ስታንዳርዶችና በምዘና መሳሪያዎች ዝግጅት ላይ ሥልጠናዎችን መስጠት፣
- የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ግንዛቤ በተጠቃሚው ዘንድ እንዲሰርፅ የግንዛቤ ማስጨበጫ አውደ-ጥናት ያካሄዳል፤ አገር አቀፍ የምክክር መድረኮችን ያዘጋጃል፤
2.5. ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች ሙያ ብቃት የፅሁፍ ምዘናና የማህደረ ተግባር መመዘኛ ማሳሪዎችን ማዘጋጀትና ማስተዳደር
- የምዘና ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤
- በተዘጋጀው የምዘና ማዕቀፍ መሰረት የጽሁፍ እና የማህደረ ተግባር ምዘና መሳሪያዎች እንዲጋጁ ማድረግ፣ የናሙና ምዘና (Pilot Test)ማካሄድና የምዘና ጥራቱን ማረጋገጥ፤
- የፅሁፍ ምዘናውን በማካሄድ የመጀመሪያ ዙር እርማት ተካሂዶ ውጤቱ በየምዘና ጣቢያው እንዲገለጽ ማድረግ፤
- የማህደረ ተግባር (Portfolio) ምዘና የሚወስዱ ተመዛኞችን በመለየት ምዘና ማካሄድ፤
- የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (Certificate) ማዘጋጀትና በክልሎች ጠያቂነት ለሚመለከታቸው እንዲደርሳቸው ማድረግ፤
2.6. በምዘና ውጤት የታዩ የተመዛኝ የይዘትና የማስተማር ሥነ-ዘዴ የዕወቀትና የክህሎት ክፍተቶችን በመተንተንና (Gap Analysis) በመለየት ግኝቱን ለባለድርሻ አካላት ማቅረብ
- የተመዛኞችን የየትምህርት ዓይነት እና የማስተማር ሥነ-ዘዴ እንዲሁም የአመራር ምዘና ክፍተቶችን (Gap Analysis) ትንተና ግኝት ከትምህርት ፖሊሲ አንጻር የተቃኘ (policy brief) ሰነድ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ፤
2.7. የሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት ሥራዎችን ጥራት ለማስጠበቅ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
- በሙያ ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት አፈፃፀም ዙሪያ የክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማ እና ግብረ-መልስ ሥራዎችን ማከናወን፤